0:00

መዝሙረ ዳዊት 134

1 የመዓረግ መዝሙር። 1 እነሆ፥ እግዚአብሔርን ባርኩ፥ በአምላካችን ቤት አደባባዬች የምትቆሙ እናንተ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሁላችሁ።

2 በሌሊት በቤተ መቅደስ ውስጥ እጆቻችሁን አንሡ፥ እግዚአብሔርንም ባርኩ።

3 ሰማይንና ምድርን የሠራ እግዚአብሔር ከጽዮን ይባርክህ።