0:00

መዝሙረ ዳዊት 130

1 የመዓርግ መዝሙር። 1 አቤቱ፥ አንተን ከጥልቅ ጠራሁህ።

2 አቤቱ፥ ድምፄን ስማ፤ ጆሮህ የልመናዬን ቃል የሚያደምጥ ይሁን።

3 አቤቱ፥ ኃጢአትንስ ብትጠባበቅ፥ አቤቱ፥ ማን ይቆማል?

4 ይቅርታ ከአንተ ዘንድ ነውና።

5 አቤቱ፥ ስለ ስምህ ተስፋ አደረግሁህ፤ ነፍሴ በሕግህ ታገሠች።

6 ከማለዳው ሰዓት ጀምሮ እስከ ሌሊት ነፍሴ በእግዚአብሔር ታመነች።

7 ከእግዚአብሔር ዘንድ ምሕረት፥ በእርሱም ዘንድ ብዙ ማዳን ነውና እስራኤል በእግዚአብሔር ይታመን።

8 እርሱም እስራኤልን ከኃጢአቱ ሁሉ ያድነዋል።